አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) ከተለያዩ ክፍል ለተውጣጡ ሰራተኞቹ ስልጠና ሰጠ፡፡ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር የሂሳብ አሰራሩን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የሚያስችለውን አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በአገሪቱ ያሉ ተቋማት የሂሳብ አያያዛቸው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) እንዲሆን በህግ በተደነገገው መሰረት አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል ማቴድ የስልጠና እና አማካሪ ኃ/የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ይህንን መሰረት ተደርጎ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነውን ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) ስልጠና ከስራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው ከተለያዩ ክፍሎች ለተውጣጡ የኅብረት ሥራ ማህበሩ ሰራተኞች መስጠት ጀምሯል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር ተከፍሎ የሚሰጥ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች 60 ሰዓት የሚወስደውን ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ስልጠናው በድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በሆኑት በአቶ ቴዎድሮስ አበበ እና በሌሎች ሙያተኞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡ (Source : Awach SACCOs fb page)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *